የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ራስ ገዝ ዩንቨርስቲዎችን ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅ ማፅደቁን ተከትሎ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ራስ ገዝ ዩንቨርስቲ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ።
ከጣቢያች ጋር ቆይታ ያደረጉት የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን፤ ጎንደር ዩንቨርስቲ ባለፉት ሁለት አመታት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።
ዩንቨርስቲው ራስ ገዝ ለመሆን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማሟላት የተለያዩ ኮሚቴዎች በማቋቋም 18 የሚሆኑ ፓሊሲዎችን ቀርፆ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።
በዚህ አመት ሙሉ ለሙሉ ዝግጅታችንን እንጨርሳለን ያሉት ዶ/ር አስራት፤ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተሞክሮዎችን በመውሰድ ከምርምር ዩንቨርስቲ የሚጠበቁበትን ለማሟላት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት አመታት 10 ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም
