የሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት መጨመሩን ተከትሎ ሚስጥራዊ መለያ ያለዉ የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ተግባራዊ ሊደረግ ነዉ፡፡

በሀሰተኛ ደረሰኝ የሚደረግ ግብይት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ QR ኮድ (በሚስጥራዊ መለያ) የተደገፈ የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ከየካቲት 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር የማንዋል ደረሰኝ ህትመቱን ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ በመስጠቱ ዜጎች ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሆነ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከነጋዴው ብዛት እና ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንፃር በአንድ የማተሚያ ድርጅት ብቻ አትሞ መጨረስ ከፍተኛ እንግልትን ያስከትላልም ብለዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ መረጃና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አሰራር ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ዜኒት አበጋዝ፤ የታክስ ደረሰኝ በሚፈቀድበት ጊዜ የደረሰኝ ህትመት ፍቃድ ፈልጎ ለመጣ ስም ብቻ ጠቅሰው ፍቃድ የሚሰጡ መኖራቸውን አንስተዋል።

ይህ መሆኑ የታክስ ማጭበርበርን ውስብስብ እያደረገ በመምጣቱ ከፍተኛ ገቢን ሊያሳጣ ችሏል ብለዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታትም የሚታተመው ደረሰኝ በQR ኮድ (በሚስጥራዊ መለያ) የተደገፈ እንዲሆን መደረጉን ወ/ሮ ዜኒት ተናግረዋል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *