ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ከአቅም በላይ እንደሆነበት ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከአቅሜ በላይ ሆኗል ያለው ፍትህ ሚኒስቴር ፤ በመሆኑም፤ ከውጭ አገራት ጋር ፤የጋራ የወንጀል የምርመራ ቡድን ለማወቅር መገደዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የ6 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አስታውቋል።

በምሥራቅና ደቡብ የአገሪቱ አካባቢዎች ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መበራከቱንና የወንጀሉን ሰንሰለት በማጥናት ዋና አስተባባሪዎችን የመለየት ሥራ መጀመሩን የሚንስቴሩ ሃላፊዎች ገልጸዋል።

ሚንስቴሩ፣ ለዓለማቀፍ የግልግል ዳኝነት ተቋማት በውጭ ምንዛሬ የሚከፈሉ ክፍያዎች መዘግየትና አንዳንድ የፖሊስ አባላት የሚያሳዩት የስነምግባር ጉድለት ለሥራው ተግዳሮት እንደኾኑበትም ሃላፊዎቹ ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል፤ በወንጀል የተገኘ ሃብትን በማስመለስ ረገድ፣ ባኹኑ ወቅት በሚንስቴሩ ሥር 292 የሃብት ምርመራ መዛግብት እንደሚገኙ አስታውቋል፤

ለአለም አሰፋ

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *