በጠለምት የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ወረርሺኞች እንዳይከሰቱ ስጋት መኖሩ ተገለጸ፡፡

በወረዳዉ የሚገኙ ተፈናቃዮችም ምንም አይነት እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡

በተፈናቃይ መጠለያዎች በአንድ ቤተሰብ ሰባት እና ከዛ በላይ የሚሆኑ አባላት ናቸዉ የሚመጡት ተብሏል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸዉ የወረዳዉ ጤና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ በይነዉ፤ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ወረርሺኞች እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ስጋት አለብን ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ምንም አይነት የህክምና ዕቃዎች እየቀረቡ አይደለም የሚሉት ሃላፊዉ፤ ከአንድ ወር በፊት የህክምና ባለሙያዎች ተመድበዉ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸዉን ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ ከነበረዉ የህክምና ዕቃዎች እጥረት በተጨማሪ ተፈናቃዮች በአንድ ቦታ ባለመቀመጣቸዉ የህክምና አሰጣጡን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበርም አንስተዋል፡፡

ከመንግስት በኩል ጊዜያዊ ከሆነ እርዳታ ዉጭ በዋናነት ተጎጂዉን ለይቶ ምንም አይነት ድጋፍ እየተደረገ አይደለም ብለዋል፡፡

መንግስት መጠለያ እና የህክምና ዕቃዎችን በማሟላት ለተፈናቃዮች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ሃላፊዉ ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *