የግብርና የምርምር ማእከላት አመታዊ ግብር እንዲከፍሉ ተጠየቁ ።

በሀገሪቱ የሚገኙ የግብርና ምርምር ተቋማት ግብርናን በምርምር ለመደገፍ የተቋቋሙ ቢሆንም ትኩረት እንዳልተሰጣቸዉ ይነሳል።

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኘሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ በአንዳንድ  የምርምር ማእከላት ለትርፍ እንደተቋቋመ ተቋሙ ታይተዉ  ግብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዉ እንደነበር አንስተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በምሳሌነትም  በሰበታ የአሳ ምርምር ማእከል 1.3 ሚሊየን ብር ለአመታዊ ግብር ክፈሉ መባሉን  ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ በተባሉ የምርምር ማእከላት ላይ የዚህ የግብር ክፈሉ አዝማሚያዎች መታየታቸውን ተናግረዋል።

የግብር ክፈሉ ጥያቄዎቹ ከህገመንግስታዊ ድንጋጌ ዉጪ ነዉ የሚሉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የግብርና ምርምር ማእከላቱ ላይ የተጣለባቸዉን አመታዊ ግብር አግባብነት የማይኖረዉ ነዉ ብለዋል።

ይህንን ለማስቆም ከክልል መስተዳድሮች ጋር ንግግሮች መደረጋቸዉን አንስተዋል።

በተያያዘም የመሬት ይዞታቸዉ አደጋ ላይ የሆነዉ የምርምር ማእከላቱ ለከተማ መስፋፋት እንቅፋት አይደሉም የሚሉት ዳይሬክተሩ ማእከላቱን  ከልማቱ ጋር አብሮ ማስጓዝ ይቻላል ሲሉ ገልፀዋል።

ጣቢያችን የመሬት ይዞታቸዉን ከተነጠቁት የጅማ ÷ የበደሌ እና የሆለታ የምርምር ማእከላት ሀላፊዎች ጋር በነበረዉ ቆይታ ይህ የይዞታ አለመጠበቅ ችግር እንደሆነባቸዉ ገልፀዋል።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *