በኢትዮጵያ በስፋት ትልቁ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ፓርክ ባጋጠመዉ የበጀት ዕጥረት ምክንያት የተፈለገዉን ያህል አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑ ተገልጿል።
የፓርኩ ኃላፊ አቶ አሰግድ ገብሬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ፤የፓርኩ ግማሽ ክፍል ዉሀማ በመሆኑ እንዲሁም፤ ጥናትም በቅርቡ ባለመደረጉ አሁን ላይ ያለዉን የፓርኩን አጠቃላይ ይዞታ ማወቅ አይቻልም ብለዋል።

በተጫሪም፤ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አለመኖር ከፓርኩ የተፈለገውን ያክል መጠቀም እንዳይቻል አድርጓል ነው ያሉት።
ፓርኩ ጥቅም ላይ እንዲዉል ለማድረግ አፍሪካን ፓርክስ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር የፓርኩን ጥበቃ ለማጠናከርና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።
በጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክ 2መቶ56 ቀጭኔዎች፣ 5መቶ50 ዝሆኖች፣ በተጨማሪም 8መቶ ሺህ በርካታ የዱር እንስሳቶች የሚኖሩበት መሆኑንም ሃላፊው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
