እስራኤል የተኩስ አቁም ቃል ኪዳኖችን ማክበር ተስኗታል አሉ ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን

እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ “የገባችውን ቃል ሳትጠብቅ ቀርታለች” ሲሉ ወቅሰዋል የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፡፡

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለጋዜጠኞች እንደተናሩት “የእስራኤል ወረራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊያበቃ ይገባል” ብለዋል። ሥራቸው “ዋና ችግር ሆኖ ቀጥሏል” ሲሉ ከሰዋል፡፡

ቱርክ እርዳታ ወደ ጋዛ እየላከች ነው ያሉት ኤርዶጋን አሁንም ዕርዳታውን ትቀጥላለች ካሉ በኃላ ፍልስጤም ነጻ የሆነች ሀገር እንድትመሰረትም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሐማስ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች በሚል ለጊዜው ታጋቾችን እንደማይለቅ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

የሐማስ ታጣቂ ክንፍ ቃል አቀባይ ቡድኑ በቅርቡ ሊለቃቸው ያሰባቸውን ታጋቾችን ለጊዜው እንደማይለቅ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሉም እስራኤል እና አሜሪካ የሐማስን ድርጊት “የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው” ብለውታል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ታግተው የነበሩትን እስራኤላውያንን ለመመለስ ቁርጠኛ እና የማያቋርጥ እርምጃ ለመውሰድ ቃል ገብተዋል።

የእስራኤል የቅርብ አጋር የሆኑት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሁሉም ታጋቾች በሚቀጥለው ቅዳሜ የማይለቀቁ ከሆነ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሊሰረዝ ይገባል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

“ሁሉም ታጋቾች ቅዳሜ ቀትር መለቀቅ አለባቸው። ሁሉም። አንድ ወይም ሁለት አሊያም ሶስት አራት ሳይሆን፤ ሁሉም” ብለዋል።

“ይህ የኔ አስተያየት ነው” ያሉት ትራምፕ “እስራኤል የፈቀደችውን ማድረግ ትችላለች” የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል።

ሃማስ የትራምፕን ዛቻ አልተቀበለውም፡፡

የሐማስ ቃል አቀባይ ለትራምፕ አስተያየት ሲሰጡ “የዛቻ ቋንቋ ዋጋ የለውም” ብለዋል።

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *