በዉጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ ጓንት እና ስሪንጅ በአገር ውስጥ መመረት መጀመራቸዉ ተገለጸ፡፡

በዉጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ ጓንት እና ስሪንጅ በአገር ዉስጥ መመረት መጀመራቸዉን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታዉቋል፡፡
አገልግሎቱ በዚህ 6 ወራት ጊዜ ዉስጥ የወባ ክትባት መድሃኒቶችን ማሰራጨቱንም ገልጿል፡፡

17 ቢሊየን ብር የሚገመት የወባ እና የማህጸን በር ካንሰር ክትባት አሰራጭቻለሁ ያለዉ አገልግሎቱ፤ 6 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማከናወኑንም አስታዉቋል፡፡

ግጭት ባለባቸዉ አከባቢዎች ወደ 8 ቢሊየን ብር የሚጠጋ መድሃኒት ማሰራጨቱን አስታዉቆ፤ በኦሮሚያ አራት ዞኖች፣ ቤንሻንጉል ክልል ፣ ጉጂ፣ የጎንደር እና ባህርዳር ከተሞች መድሃኒቶቹ የተሰራጩባቸዉ አከባቢዎች መሆናቸዉን ገልጿል፡፡

14 ቢሊየን ብር የሚያወጡ መድኒቶች በግዥ ወደ መጋዘን ገብተዋል ያሉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ ከዚህ ዉስጥ 7 ቢሊየኑ በእርዳታ የተገኘ ነዉ ብለዋል፡፡

በመጋዘን ዉስጥ 85 በመቶ የመድሃኒት ክምችት መኖሩን አንስተዉ፤ 25 በመቶዉ በአዲስ አበባ የሚከፋፈል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

የየካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *