በሀገሪቱ የሚታየው የንግድ ባንኮች እድገት ጤናማ አይደለም ተባለ።

በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች በተናጥል የሚያደርጉት እድገት እና ግስጋሴ ዘርፉ ጤናማ ደረጃ ላይ አለመሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።

ባንኮቹ በተናጠል እያሳዩ ያሉት ዕድገት የተለያየ ሆኖ መቀጠሉ ጤናማ አለመሆኑን የነገሩን የባንክ ባለሞያው አቶ ገመቹ ብርሀኑ፤ ባንኮች የባላአክሲዎኖቻቻውን አቅም በሚገባ ማሳደግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባንኮች በዘንድሮው የሒሳብ ዓማት አጋማሽ በአብዛኞቹ በቁልፍ የባንክ ሥራ መመዘኛዎች ዕድገት ማሳየታቸውን ቢገልፁም በመካከላቸው ያለው ልዩነት ያለ ልክ መስፋቱ ለዘርፉ ትልቅ ስጋት መሆኑን አንስተዋል።

አቶ ገመቹ ባንኮቹ እስከ ቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት ድረስ የሚጠበቅባቸውን የ 5ቢሊየን ካፒታል ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች ቢጠበቅባቸውም፤ አንዳንድ ባንኮች እስካሁኑ ባላቸው አፈፃፀም የሚጠበቅባቸውን ካፒታል የሚያሟሉ አይመስሉም ሲሉ ስጋታቸውን ነግረውናል።

በኢትዮጵያ ሁሉም የንግድ ባንኮች ተመሳሳይ ሥራ የሚሠሩ በመሆኑ ከዚህ ዓይነት አመለካከት ወጥተው አሰራራቸውን ማዘመን አለባቸው የሚሉት ባለሞያው፤ ይህ ካልሆነ ግን ተወዳዳሪ ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ስጋታቸውን አንስተዋል፡፡

የባንክ ባለሞያው፤ በተለይ ካፒታላቸው አነስተኛ የሆኑ ባንኮች ካፒታላቸውን ለማሳደግ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው አንዱ መፍትሔ ባለአክሲዮኖቻቸውን አሳምነው ካፒታላቸውን ከፍ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙት ባንኮችን የ2017 ግማሽ የሒሳብ ዓመት አፈጻጸም እንደሚያሳየው፣ በገበያ ውስጥ የሚገኙ 32 ባንኮች አጠቃላይ የሀብት መጠን ከአራት ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን የባንኮቹ ሪፖርት ያሳያል፡፡

በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ረገድም የሀገሪቱ ባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ23 በመቶ በላይ ዕድገት አሳይቷል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ ግማሽ ላይ የሁሉም ባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብከ2.9 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱንም ከባንኮቹ መረጃ ተመልክተናል፡፡

ለአለም አሰፋ

የየካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *