ሀማስ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ታጋቹቹን እንደሚለቅና የተኩስ አቁምም ስምምነቱ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል ።
ከቀናት በፊት ሐማስ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች በሚል ለጊዜው ታጋቾችን እንደማይለቅ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡
የሐማስ ታጣቂ ክንፍ ቃል አቀባይ ቡድኑ በቅርቡ ሊለቃቸው ያሰባቸውን ታጋቾችን ለጊዜው እንደማይለቅ ተናግረው ነበር ፡፡
ይህንን ተከትሉም እስራኤል እና አሜሪካ የሐማስን ድርጊት “የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው” በማለት ጋዛ ላይ ዳግም ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ሲያስጠነቅቁ ነበርለ፡፡
ግብፅ እና ኳታር በጋዛ ሰርጥ በእስራኤል እና ሐማስ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳይቋረጥ ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።
እስራኤል በበኩሏ ስለ ስምምነቱ ቀጣይነት እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም።
እስከ ቅዳሜ እኩለ ቀን ድረስ ሃማስ ታጋቾችን ሙሉ በሙሉ ካለቀቀ ስምምነቱ ውድቅ ይሆናል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራንፕና የእራኤሉ ፕሬዚዳን ቤንጃሚን ኔታኒያሁ መናገራቸው ይታወሳል።
ልኡል ወልዴ
የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
