የዩክሬኑን ጦርነት ለመቋጨት ያለመዉ የሰለም ንግግር በሳዉዲ አረቢያ መዲና ሪያድ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የሰላም ንግግሩ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነዉ እየተካሄደ የሚገኘዉ፡፡
በመድረኩ ላይ የሩሲያን ልዑክ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ሲመሩት በአሜሪካ በኩል ደግሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮና የደህንነት አማካሪዉ ሚካኤል ዋልትዝ ይገኙበታል፡፡
ይሁን እንጅ የግጭቱ ባለቤት የሆነችዉ ዩክሬን በመድረኩ ላይ አለመጋበዟ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ፡፡
ከአዉሮፓ አገራትም የተጋበዘ እንደሌለ አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ እኛ ያልተሰተፍንበትን የሰላም ንግግር አንቀበልም ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡
የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
