ኤሲ ሚላን እና አታላንታ ከሻምፒየንስ ሊግ ውጪ ሲሆኑ ባየር ሙኒክ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ ፡፡

የሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ የጣልያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ከፌይኖርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኤሲ ሚላንን ግብ ሳንቲያጎ ሂሚኔዝ ሲያስቆጥር ካራንዛ ፌይኖርድን አቻ አድርጓል።

የኔዘርላንዱ ክለብ ፌይኖርድ የደርሶ መልስ ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ አስራ ስድስቱን ተቀላቅሏል።

በጨዋታው የኤሲ ሚላኑ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲኦ ሄርናንዴዝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

የሰባት ጊዜ የሻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ ኤሲ ሚላን ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ ሆኗል።

ክለብ ብሩጅ 16ቱን ለመቀላቀል ባደረጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አታላንታን በደርሶ መልስ ድምር ውጤት 5-2 በማሸነፍ የ16ቱን ጥሎ ማለፍ ተቀላቅለዋል።

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባየር ሙኒክ ከሴልቲክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የሴልቲክን ግብ ኩን ማስቆጠር ሲችል አልፎንሶ ዴቪስ በመጨረሻ ደቂቃ የባየር ሙኒክን ወሳኝ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ባየር ሙኒክ ሴልቲክን በድምር ውጤት 3ለ2 በማሸነፍ አስራ ስድስቱን ተቀላቅለዋል።

በሌላ ጨዋታ ቤኔፊካ ሞናኮን በድምር ውጤት አሸንፈው አሰራ ስድስት ውስጥ መቀላቀል ችለዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *