12ኛ ቀኑን በያዘዉ የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ከ4መቶ7ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እየተደረገ በሚገኘዉ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እስካሁን 4መቶ7 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል።

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአዲስ አበባ እና በክልል የጀመረዉን ስራዉን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር እንደሚስፈልገው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ከየካቲት 01 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሰይፉ በኢቢኤስ ዩቲዩብ ቻናል እየተደረገ በሚገኘዉ የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሀግብር ላይ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

እየተካሄደ ባለው በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እየተገነቡ ለሚገኙ ህንጻዎች ሴራሚክስ፣ የኤሌትሪክ ዕቃዎች፣ የውኃ ቧንቧዎች ፣ የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና የመሳሰሉትን መግዣ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

መቄዶንያ በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሻሸመኔ፣ አድዋ፣ ባህርዳር እና ሌሎችንም ጨምሮ በአጠቃላይ በ44 ከተሞች ቅርንጫፍ በመክፈት ስራውን በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጣይም በወሊሶ፣ ሱልልታ፣ ሰበታ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሆሳዕና፣ ዲላ፣ ጂግጂጋ፣ እና በሌሎች ከተሞች ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ8ሺህ በላይ የሚሆኑ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ፣ መመገብ እና መፀዳዳት የማይችሉ የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማንን በማገዝ ላይ የሚገኝ ተቋም ነዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *