‹‹ስለህዳሴ ግድብ ለማዉራት ወደሌሎች ሀገራት አንሄድም›› አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 98.13 በመቶ መድረሱ ተናግረዋል፡፡ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት መሆኑን የጠቀሱት የዉሃና ኢነርጅ ሚኒስትሩ ፤ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለማዉራት ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ እንጂ እኛ ወደሌላ አንሄድም ሲሉ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናግረዋል፡፡

ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የመደራደር አቅምን ፈጥሯል ነዉ ያሉት ሚኒስትሩ ህዳሴ ግድብ ሲገነባ የታችኛዉን ተፋሰስ ሃገራት በማይጎዳ ይልቁንም በሚጠቅም መንገድ ነዉ ታስቦ የተሰራዉ ነው ብለዋል፡፡

ግድቡ የኢትዮጵያን የመልማት መብት የሚያረጋግጥና የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያሳድግ መሆኑንም አንስተዋል።

ለተስተካከለ የውሃ አቅርቦት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅንና ድርቅን ለመከላከል ይረዳልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአለም ሃገራት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እርዳታን ባቋረጡበት ወቅት እና የተለያዩ ሀገራት ሴራዎች በሸረቡባት በዚህ ጊዜ የህዳሴ ግድብን እዉን ማድረጓ ትልቅ አቅምን ፈጥሮላታል ሲሉ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢታፋ ተናግረዋል፡፡

ልአኡል ወልዴ

የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *