ሊቨርፑል ከፒኤስጂ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በሀርቬይ ኤሊዮት ብቸኛ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ሊቨርፑል የፒኤስጂን በሁሉም ውድድሮች የ22 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ግስጋሴ መግታት ችለዋል።
ሊቨርፑል በዚህ ሲዝን በቻምፒዮንስ ሊጉ በ 9 ጨዋታ 8 አሸንፈዋል ።
ባየር ሙኒክ በበኩሉ ሀሪ ኬን ሁለት እና ጀማል ሙሲያላ ባስቆጠሯቸው ግቦች ባየር ሌቨርኩሰንን 3ለ0 አሸንፈዋል።
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በውድድር ዘመኑ ለባየር ሙኒክ 31ኛ ግቡን አስቆጥሯል።
ባርሴሎና ከቤኔፊካ ጋር ጨዋታውን አድርጎ በራፊና ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ኢንተር ሚላን ከፌይኖርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ማርከስ ቱራም ማስቆጠር ችለዋል።
አርጀንቲናዊው ተጨዋች ላውታሮ ማርቲኔዝ በ 18 ግቦች የኢንተር ሚላን የምንግዜም የሻምፒየንስ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
