የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት እንዳስታወቀው በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሱዳን ጥምር መንግስት ማቋቋም ችግሩን የሚባብሰው በመሆኑ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገው አስታውቋል፡፡
የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ድጋፍ ሰጪ ኃይል እና የሱዳን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በሃገሪቱ ጥምር መንግስት ለመመስረት ኬኒያ ላይ ስምምነት ተፈራርመው የነበረ ሲሆን ይሄንን ስምምነት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውድቅ አድርጎታል፡፡
በጸጥታው ምክር ቤት ስምምነቱ ውድቅ መደረጉን በደስታ ተቀብያሁ ብሏል የሱዳን መንግስት ፡፡
የሱዳን መንግስት አያይዞም ኬኒያ የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ድጋፍ ሰጪ ኃይል እና ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ጥምር መንግስት እንዲመሰርቱ በማፈራረምና የሱዳን ሉአላዊነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማሴር ከሷታል፡፡
ኬኒያ በበኩሏ በሱዳን ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም ከተባበሩት መንግስታትና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመሆን ጥረት እያደረገች እንደሆነ ምላሽ ሰታለች ሲል የአናዱሉ ዘግቧል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
