የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሶማሊያ በማዕከላዊ ሸበሌ ክልል በሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ቁልፍ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ማድረሱን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር አስታውቀዋል፡፡
የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃዲር መሀመድ ኑር እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኃይል በአልሸባብ ምሽግ ላይ የሚሳኤል ጥቃት የተፈጸመው ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ነው።
“ያለ መንግስት እውቅና በሶማሊያ ምንም አይነት የአየር ጥቃት ሊፈፀም አይችልም” ብለዋል።
ይሁን እንጂ በኦፕሬሽኑ ስለደረሰው ሞት ወይም ጉዳት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ሚኒስትሩ የአንካራው ስምምነት በአል-ሸባብ ላይ ለሚወሰዱ የጋራ ጥረቶች ማዕቀፍ መሆኑን በመጥቀስ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ የፀጥታ ትብብር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሰሞኑን የአልሸባብ ወታደራዊ ይዞታዎችን መደብደቡን ሶማሊያ ጋሪዳያን መዘገቡ ይታወሳል።
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
