የቀድሞዉ የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ፤ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ ጊዜ በፈጀን ቁጥር ሃማስ የበለጠ ለመደራጀት ጊዜ ያገኛል ብለዋል፡፡
ለቀጣዩ ዙር ድርድሮች ተጀምረዉ ማለቅ ከነበረባቸዉ ጊዜ ዘግይተዋል ነዉ ያሉት፡፡
በተለያየ ጊዜ ዋጋ ከመክፈል በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ መክፈል ጥቅሙ ለእስራኤል ነዉ ብለዋል፡፡
ከመጨረሻው ውል ጀምሮ ከ30 በላይ ታጋቾችን አጥተናል ያሉት ቤኒ፤ ስምምነቱ በዘገየ ቁጥር የቀሩት ታጋቾችን የበለጠ አደጋ ላይ የሚጥል ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሁለተኛው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
ከእንደዚህ ዓይነት ንግግሮች በፊት ሃማስ ስምምነት እንዲያደርግ ጥሪ ቢያቀርቡም፤ሃማስ እርምጃዉን ውድቅ አድርጎታል።
ይሁን እንጂ የኔታያሁ ቢሮ በዚህ ሳምንት ለውይይት ወደ ኳታር ቡድን እንደሚላክ አስታዉቋል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
