የመንገድ ደህንነት ባለስልጣን 554/2016 መሰረት የሶስተኛ ወገን የኢንሹራንስ ህግ አሻሽሎ በሀገር አቀፋ ደረጃ ወደ ተግባር መግባቱን ጣቢያችን ሰምቷል።
በመንገድ ደህንነትና የመድህን ፈንድ አገልግሎት የመንገድ ደህንነትና የአቅም ግንባታ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሃንስ ለማ፤በተሻሻለው የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት መመርያ መሰረት ለአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት ቀደም ሲል 2 ሺህ ብር የሚከፈል ሲሆን አሁን ወደ 15 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል ነው ያሉት።
ቀድሞ የነበረው 2 ሺህ ብር አሁን ባለው ሁኔታ ተገቢውን ህክምና እንኳን ሊሰጥ ይቅርና ካርድ ለማውጣት እንኳን አይበቃም ሲሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሽከርካሪዎች የሞት አደጋ ሲያደርሱ በፊት የሚከፈለው 40 ሺህ ብር በማሻሻያው ወደ 250 ሺህ ብር ማደጉን አስታውቋል።
ምንም እንኳን ህይወትን በገንዘብ መተካት ባይቻልም ለጊዜያዊነት ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ካሳ እንዲሆን ነው ብለዋል።
አካል ጉዳት ያደረሰም በተመሳሳይ 40 ሺህ ብር የቅጣት ክፍያ ይፈፅም የነበረው በአዲሱ ማሻሻያ መሰረት250 ሺህ ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አቶ ዮሃንስ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰንነው ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር እንዲሁም ከተጎጂዎችና ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተደረገ ውይይት ነው ብለዋል።
በፊት የነበረው የህክምና ፣የአካል ጉዳት እንዲሁም የሞት ቅጣት አሁን ካለው የሀገሪቱና ከአህጉሪቱ ነባራዊ ሁኔታ የማይጣጣም በመሆኑ ተሻሽሎ ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል።
ልኡል ወልዴ
መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም
