በደቡብ አፍሪካ በመጪው ሚያዚያ ወር ከፍተኛ የነዳጅ ቅናሽ ሊኖር እንደሚችል ተገለጸ

ሴንትራል ኤነርጂ በተባለው ተቋም መረጃ መሰረት የደቡብ አፍሪካ አሽከርካሪዎች በመጪው ሚያዚያ ወር የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ እፎይታ ሊያገኙ እንደሚችሉ አስነብቧል፡፡

የነዳጅ ዋጋ በሊትር ከ85 እስከ 98 ሳንቲም ፡፡ ናፍጣ ከ86 እስከ 87 የደቡብ አፍሪካ ሳንቲም ቅናሽ ሊያደርግ እንደሚችል አይ ኦ ኤል የተባለው የሃገሪቱ ድርጅት ገልጹል፡፡

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከመስከረም 2024 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነዳጅ በርሜል ከ ሰባ ዶላር በታች እንደተሸጠ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም አሜሪካ በዋና ዋና የንግድ አጋር ሃገራት ላይ በጣለችው ታሪፍ ምክኒያት የተፈጠረው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ያስከተለው እንደሆነ የኦል አፍሪካ ነው ዘገባ አስታውሷል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *