በአዲስ አበባ ከተማ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተገልጿል

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በአሁን ጊዜ በጥናት የተደገፈ መረጃ ባይኖርም አንዳንድ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም ሲል አስውቋል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት ትኩረት የሚሰጣቸው ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ትኩረት እንደሚፈልጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጤና ማጎልበት እና በሽታ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር አቶ ጌቱ ቢሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል የአኗኗር ዘይቤያችን መቀየር መሆኑን አንስተዋል፡፡

አንዱ ደግሞ የአመጋገብር ስርአታችን መቀየር ነው ብለዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍም ከህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያችም ተላላፊ ስላልሆኑ በሽታዎች ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ሀላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *