ከዚህ በፊት እነዚህ ተቋማት ከትምህርት ቤት በመቶ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሆኑ አዋጅ መኖሩ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ በመዲናዋ የሚገኙ ከሁለት ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ትንባሆ የማይጨስባቸው እና የማይሸጥባቸው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ይህንን የነገሩን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ልማት እና ፀረ-ወባ ማህበር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት ናቸዉ፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ማህበራቸዉ በመዲናዋ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ሱስ የሚዘወተርባቸዉ ተቋማት ከትምህርት ቤቶች በመቶ ሜትር ርቀት ዉስጥ እንዲሆኑ ያዝ ነበር፤ ወደ ፊት ግን ይህን ቁጥር ወደ 5መቶ ሜትር ከፍ ለማድረግ በዕቅድ ደረጃ መታሰቡን ሰምተናል፡፡
በሀገራችን ከ40 በመቶ በላይ የሞት ምጣኔ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ነዉ፡፡
በሀገራችን ካለው የሞት ምጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ሞት ሲሆን፤ትንባሆ ደግሞ ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
