የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአፍጋኒስታን ተልዕኮ ግዳጁን ለ1 አመት አራዘመ

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በአፍጋኒስታን ያለውን የእርዳታ ተልእኮ ተግባርና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ሳይለውጥ የቆይታ ጊዜውን በሙሉ ድምፅ አራዝሟል።

የውሳኔ ሃሳቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ተልዕኮን በአፍጋኒስታን እስከ መጋቢት 17 ቀን 2026 ድረስ ያራዝመዋል።

ሁሉም የሚመለከታቸው የአፍጋኒስታን የፖለቲካ ተዋናዮች እና ባለድርሻ አካላት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተዋናዮች የምክርቤቱን የግዳጅ አፈፃፀም እንዲተባበሩ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ተያያዥ ሰራተኞች ደህንነትን እና የመንቀሳቀስ ነጻነትን እንዲያረጋግጡ ያሳስባል ብሏል፡፡

15 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአፍጋኒስታን ስላለው ሁኔታ እና ስለ ተልዕኮዉ አፈፃፀም የሩብ ዓመት ሪፖርቶችን እንዲያቀርቡ ጠይቋል ፡፡

በካቡል የተመሰረተው የግዳጅ ተልዕኮዉ ወደ 1ሺህ2መቶ የሚጠጉ ሰራተኞች አሉት ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *