ሃማስ እንዳስታወቀው እስራኤል ምሽቱን በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 3 መቶ ሰላሳ ሰዎች ሞተዋል፡፡
የእስራኤል ጦር እንደገለጸው ከሃማስ ጋር ሲደረግ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነቱን የማራዘም ውይይት ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ የተፈጸመ ከባድ የአየር ድብደባ ነው ብለዋል፡፡
ሁለቱ አካላት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው ከነበረው ከጥር 19 ወዲህ የተፈጸመ እጅግ ከባድ የአየር ድብደባ እንደሆነ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘግዋል፡፡
በጋዛ የሚኖር አንድ የአይን እማኝ እደገለጸው በጋዛ ዳግም የገሃነብ በሮች ተከፍተዋል ብሉዋል፡፡
የፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ጽ/ቤት እንደገለጸው እስራኤል ከዚህም በኃላ በሃማስ ላይ የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ ትቀጥላለች ብሏል፡፡
ጽ/ቤቱ ሐማስ ያገታቸውን ዜጎች እንዲለቅ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆኑና የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት የማራዘም ሁኔታንም ባለመቀበሉ እርምጃውን መውሰዷን አስታውቋል፡፡
ሐማስ በበኩሉ እስራኤል እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ንጹሃን ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው ሲል ከሷል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም
