ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በባህርዳር ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ቤተሰቦች የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡

በባህርዳር እና ጎንደር ከተሞች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ 6ወራት የነጻ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠቱንም አስታዉቋል፡፡

በሁለቱ ከተሞች ለሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች የኮምፒዉተር፣ የዋይፋይ ራዉተሮች እና የ 6 ወራት ነጻ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠቱን ኩባንያዉ ገልጿል፡፡

ኩባንያዉ ያደረግኩት ድጋፍ በክልሉ ላሉ ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነዉ ብሏል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትምህርትን ከመደገፍ በተጨማሪ በባህርዳር ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 1መቶ ቤተሰቦች 150ሺህ ብር የሚገመት የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ማድረጉንም አስታዉቋል፡፡

በጤናዉ ዘርፍ ያደረገዉ ድጋፍ ለህክምና አቅም የሌላቸዉን ቤተሰቦች ለአንድ ዓመት መደጎም የሚችል ነዉ፡፡

በባህርዳር ለሚገኙ 3 ትምህርት ቤቶች 30 ኮምፒዉተሮችን፣ 6 የዋይፋይ ራዉተሮችን እና የ6 ወራት ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ በጎንደር ደግሞ ለ2 ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *