የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች ከጋዛ ለቀዉ እንዲወጡ ግዳጅ ማስቀመጡ ተነገረ

ጦሩ በጋዛ ከባድ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ነዋሪዎች ለቀዉ እንዲወጡ አዟል፡፡

የእስራኤል ጦር ቢያንስ ከ4 መቶ በላይ ፍልስጤማውያንን ከገደለ እና 5መቶ62 ሌሎችን ቁስለኛ ካደረገ በኋላ፤በጋዛ የሚገኙ ነዋሪዎች አከባቢዉን ወዲያዉ ለቀዉ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የእስራኤል ጦር ሰራዊት በአሸባሪ ድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሟል። እነዚህ ስፍራዎችም አደገኛ የጦር ቀጠናዎች በመሆናቸዉ፤ሲቪሎች ወደ ምዕራብ ጋዛ ወይም ካን ዮኒስ ወደሚገኙ መጠለያዎች መሄድ አለባቸው ሲሉ የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

ትዕዛዙ የተሰጠዉ እስራኤል በግዛቱ ካደረሰችዉ ከባድ ጥቃት በኋላ ነዉ፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ ሃማስ ፤ የኔታኒያሁ መንግስት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰውን የሁለት ወራት የተኩስ አቁም ስምምነት ለመቀልበስ መፈለጉን አሳይቷል ብሏል፡፡

በጋዛ የደረሰዉ ጥቃት እና ከቦታዉ እንዲለቁ የተሰጠዉ ትዕዛዝ፤ በተኩስ አቁም ስምምነቱ ፍልስጤማውያን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከተፈቀደላቸው ሳምንታት በኋላ የተፈጠረዉን አንጻራዊ መረጋጋት የረበሸ ነዉ ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡

በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 413 የደረሰ ሲሆን ፤ግብጽ፣ ቱርክ፣ ቻይና እና ሩሲያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በጋዛ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።

ሰንፔር እንዳለዉ

መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *