የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከከል፤
መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን ነው መንግሥት እና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በኾነ መንገድ ተነጋግሮ የመፍታት ባሕል ማጎልበት ላይ በተሰሩ ስራች የተገኘ ውጤት ቢብራር
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰላም መሰመሰር ለማስያዝ በስምምነቱ መሠረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
አሁን ላይ የመንግስት ሰራተኛ እና በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎች የኑሮ ውድነት ጫና አለባቸው፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ ምን ታስቧል?
የተለያዩ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት እየተደረገ ያለው ሂደት ምን ላይ ይገኛል የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል፡፡
በተጨማሪ የእስረኞች አያያዝ እና የፍርድ ሂደት ፤ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው የሚሉም ይገኝበታል፡፡
በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመሰሉም፤ መንግሥት ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት ተማሪዎች እንዲመለሱ ማድረግ ያልቻለው ለምንድን ነው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ ሌሉች ጥያቄዎች ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤት አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየት ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
