ኢትዮጲያ በስምንት ወራት ውስጥ ቡናን ወደውጭ በመላክ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስተሩ ተናግረዋል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
በሚቀጥሉት 4 ወራት በታቀደው ልክ የሚፈፀም ከሆነ ቡናን ኤክስፖርት በማድረግ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ዶክተር አቢይ አህመድ ገልፀዋል
ከለውጡ ማግስት ከቡና የሚገኘው የውጭ ገቢ 700 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለፈው አመት ብዙ እምርታ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት 1.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ተችሎል ብለዋል
በዚህም ኢትዮጲያ በታሪክ ትልቁ የቡና ኤክስፖርት ያገኘችበት አመት ሆኖ ማለፉን አስታውቀዋል
ከቡና የውጭ ገቢ ከፍተኛ ገቢ መገኘቱ በዘርፉ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ስራ መስራቱን ያሳያል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አንስተዋል፡፡
አቤል እስጤፋኖስ
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
