ወጣቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ስብሰባ ሊካሄድ ነው።

ከ 2 ሳምንት በኋላ የፓን-አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባዔ በመዲናዋ ይካሄዳል።

ስብሰባውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት እና ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል።

ከ54ቱም የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 2መቶ8 ወጣቶች እና ከአገር ውስጥ ደግሞ 1ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሏል።

በአፍሪካ ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ዜጎች 70 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ።

ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ያሉ ወጣቶች ቁጥር ደግሞ 1.2 ቢሊየን ነው።

ይህ ቁጥር በ7 በመቶ አድጎ ወደ 1.3 ቢሊየን ከፍ ሊል እንደሚችል ተገልጿል።

ይህም የዓለምን ህዝብ 16 በመቶ ይይዛል።

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *