በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡን የፖለቲካ ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ዶ/ር የእዮብ ዘውዴ፤ የኢትዮጲያ አካሄድ ጥንቃቄን ያማከለ መሆን እንደሚገባው ነግረውናል።
ዶ/ር የእዮብ በተለይ አካሄዱ አለም አቀፍ ህግጋትች በማክበር እንደሆነ አንስተው ይህ ደግሞ እሱን ተከትሎ ለሚመጡ ችግሮች እንደ መፍትሄ ሆኖ ሚያገልግል ነው ብለውናል፡፡
በተለይ ሂደቱ ጥንቃቄ በተሞላበት እና ሌላ ጦሶችን ይዞ በማይመጣ መልኩ መሆን አለብት ሲሉም ነግረውናል፡፡
የባህር እና ወድብ ጥያቄዎቻችን ከጥንት ከንጉሱ እና ከመንግስቱ ጀምሮ የነበረ ጥያቄ ነው ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከቀይ ባህር እንድትገፋ ታስቦ የተደረገ እንደበነበር አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ልምታደረገው የቀይባህር ተዋሳኝነት ሂደት ላይ ምንም አይነት ክፍት መተው እንማይገባ የሚያነሱት ባለሞያው “የውስጥ ሰላማችን ዘላቂ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል”፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ እያቀረበች ያለው የቀይ ባህርን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ተገቢና ወቅቱን ያገናዘበ መሆኑን በማነሳት የቀይ ባህር ጉዳይ የአንድ መንገስት ወይ ፓርቲ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሙሉ ህዝብ በመሆኑ ጥያቄው መቼም ቢሆን የሚቀር አይደልም ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ለአለም አሰፋ
መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
