የአዉሮፕላን አብራሪዉ ፓስፖርቱን በመርሳቱ በረራዉን ለመቀየር የተገደደዉ የአሜሪካ አየርመንገድ አዉሮፕላን

ከአሜሪካ ወደ ቻይናዋ ሻንጋይ በመጓዝ ላይ የነበረ አዉሮፕላን፤ አብራሪዉ ፓስፖርቱን በመርሳቱ ምክንያት ሳንፍራንሲስኮ ላይ ለማረፍ ተገዷል፡፡

የአየርመንገዱ ቃል አቀባይ እንዳሉት አብራሪዉ ፓስፖርቱን ባለመያዙ ምክንያት የበረራ አቅጣጫዉ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ተቀይሯል፡፡

ቅዳሜ ዕለት 2መቶ57 ተጓዦችን አሳፍሮ ከአሜሪካዋ ሎስአንጀለስ ዓለም ዓቀፍ አየርማረፊያ የተነሳዉ አዉሮፕላኑ ፤ ለሁለት ሰዓታት ከተጓዘ በኋላ ቀን 11 ሰዓት ላይ ሳንፍራንሲስኮ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል፡፡

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ፤ አዉሮፕላኑ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ አዲስ የበረራ ቡድን መጥቶ አዉሮፕላኑን እንደተቀበለ እና ተጓዦችም ማታ ላይ ወደ ቻይና ሻንጋይ በሰላም መድረሳቸዉን አስታዉቀዋል ሲል ዘ ኢንዲፔንደንት ነዉ የዘገበዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *