የሩሲያ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት 12 ሰአታትን የፈጀ የአሜሪካ ሩሲያ ውይይት ሳዑዲ አረቢያ ላይ ከተደረገ በኃላ በዛው አሜሪካ ከዩክሬን ጋር ውይይቱዋን ትቀጥላለች፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ እንዳሉት የአሜሪካና ሩሲያ ውይይቶች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ የአሜሪካና ዩክሬን ውይይት ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የሩሲያና አሜሪካ ውይይት ዋንኛ አጀንዳ የጥቁር ባህር የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ እንደሆነ የተዘገበ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶስት አመት የቀጠለውን የሁለቱን ሃገራት ጦርነት በፍጥነት ለማስቆም ግፊት እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም በሃገራቱ መሃል እየተደረጉ ያሉት ተደጋጋሚ ውይይቶች ወደሚታሰበው የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ መንገድ ይጠርጋሉ ሲል የዘገበው ኬይቭ ፖስት ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
