እስራኤል በጋዛ የሚገኙ ከ1መቶ በላይ መኪኖችን ኢላማ ማድረጓን ገለጸች፡፡

የእስራኤል ጦር ከአገር ዉስጥ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ፤ሃማስ በጥቅምት 7ቱ ጥቃት ድንበር ጥሶ ለመግባት ተጠቅሞባቸዋል የተባሉ ከ1መቶ በላይ ፒክ አፕ መኪኖች ላይ ኢላማ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

የእስራኤል ጦር እና የእስራኤል የአገር ዉስጥ ደህንነት ኤጀንሲ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ መኪኖቹ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም እና የጦር መሳሪያዎችን ለማዘዋወር ጥቅም ላይ ዉለዋል ብለዋል፡፡

የእስራኤል ጦር ሃማስ ለምሽግነት ይጠቀማቸዋል በሚል በተደጋጋሚ የንጹሃንን ንብረቶች እና መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም መስጊድ እና ሆስፒታሎችን ሲያወድም ቆይቷል፡፡

ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በእስራኤል ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 50ሺህ ፍልስጤማዊያን ህይወታቸዉ ሲያልፍ፤ ከ1መቶ13ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *