የታይላንዷ ዋና ከተማ ባንኮክ ፖሊስ እንዳስታወቀው በባንኮክ በተከሰተው 7 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል በተለካ ርዕደ መሬት በርካታ ህንጻዎች መደርመሳቸውን ገልጹዋል፡፡
በማህበራዊ ደረገጾች ላይ የሚዘዋወሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ እንደሚታየው ህንጻዎች እየተደረመሱ ፤ እጅግ በርካታ ሰዎችም እራሳቸውን ለማዳን ሲሸሹ ታይተዋል፡፡
እስካሁን በአደጋው ስለተጎዱም ሆነ ህይወታቸው ስላለፈ ሰዎች የተባለ ነገር የለም፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ከጎረቤቱዋ ማይናማር ሳይነሳ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
የታይላንዱዋ ከተማ ባንኮክ 17 ሚሊየን ዜጎች የሚኖሩባት ሲሆን አብዛኞቹም በሰማይ ጠቀስ ፎቆች የሚኖሩ ከመሆናቸው አንጻር ከባድ አደጋ እደተደቀነባት የዘገበው አይሪሽ ኤግዛማይነር ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
