መጋቢት 24ን ምክንያት በማድረግ ባለፉት ሰባት አመታት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ተከፈተ።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ ያስመዘገበውን ድሎች የሚያሳይ ኤግዚብሽን፤በኦሮሚያ ባህል ማዕከል በዛሬው ዕለት ተከፍቷል።

ኤግዚቢሽኑ በኦሮምያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ከዛሬ መጋቢት 25 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሞ የባህል ማዕከል ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በዚህ ኤግዚቢሽን የሸገር ከተማን ጨምሮ ሁሉም የኦሮሚያ የሴክተር መስሪያቤቶች ባለፉት ሰባት አመታት ያከናወኗቸውን ተግባራት ለህዝቡ እንደሚያሳዩ ተገልጿል።

በመክፈቻ መርሃግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የፌድራልና የክልል ከተሞች ሃላፊዎች፣የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት ተገኝተዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን፤ የዚህ ኤግዚቢሽን አላማ ባለፉት ዓመታት የተሰሩትን ስራዎች ለህዝብ በግልፅ በማስረዳት በኩል ሚናው ትልቅ ነው ብለዋል።

በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በኩል ከፍተኛ እድገትና መሻሻሎች መታየታቸውንም አፈጉባኤዋ ጠቅሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፤ያለፉት 7 ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት መሆኑን ጠቅሰው የተገኘውን እድልና የአሰራር ሂደት ዘላቂ ማድረግ እንዲሁም አንድነታችንና ሰላማችን ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።

ክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም፣በመንከባከብ እንዲሁም የስራ ባህልን በማሻሻል እና ወደ ቴክኖሎጂ በመቀየር በኩል ሰፊ ስራ መሰራቱንም አብራርተዋል።

ልኡል ወልዴ

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *