በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የዋልያ አይቤክስ ቁጥር መመናመኑን ሰምተናል።
በአገራችን አሁን ላይ 3መቶ6 ዋልያዎች ብቻ መቅረታቸዉን የኢትዮጲያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታዉቋል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን፤ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው የዋልያ አይቤክስ በተለያዩ ጊዜያት በሚስተዋሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት ህልውናው ለአደጋ ተጋልጧል ብለዋል።
ሕገ ወጥ አደን መበራከት፣ ልቅ ግጦሽ መኖር፣ በአካባቢው ሕገ-ወጥ የቤት ግንባታ መኖር እና ያልተቀናጀ የልማት ስራዎች ለዋሊያ ቁጥር መቀነስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት የዋሊያ አይቤክስ ብዛት 8መቶ65 ደርሶ እንደነበር ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ ምክንያቶች አሁን ላይ 3መቶ6 ዋሊያዎች ብቻ መቅረታቸውን አስታዉቀዋል።
አቤል እስጢፋኖስ
መጋቢት 29ቀን 2017 ዓ.ም
