የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እስራኤል በፖሊዮ ክትባቶች ላይ ገደብ መጣሏን ተከትሎ በክልሉ የጤና ቀዉስ ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡
እስራኤል የፖሊዮ ክትባቶች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ መከልከሏ ወረርሽኙን እንዲስፋፋ የሚያደርግ የጊዜ ቦምብ ነው ሲል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታዉቋል፡፡
ይህ ፖሊሲ በጋዛ ሰርጥ ያሉ ህጻናትን በተዘዋዋሪ ዒላማ ለማድረግ የታሰበበት ነዉ ሲል አክሏል፡፡
ሚኒስቴሩ የፖሊዮ ክትባቶች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ ገደብ ማስቀመጥ ባለፉት ወራት በክልሉ በሽታዉን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ የሚጥል ነዉ ሲል አስጠንቅቋል።
በጋዛ የክትባት እገዳዉ ከቀጠለ ከ 6መቶሺህ ህጻናት በላይ ለዘለቄታዊ እና ከባድ የአካል ጉዳት የተጋለጡ ይሆናሉ ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በጦርነት ለተጎዳው የጋዛ ነዋሪ የፖሊዮ ክትባቶችን እንድትሰጥ ጫና እንዲያደርግ ተማጽኗል።
በተጨማሪም በሁሉም የጋዛ አካባቢዎች ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ በጋዛ ውስጥ ሰላማዊ መተላለፊያዎች እንዲኖሩ ጠይቋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
