ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በመሆን የስልጣን ርክክብ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታዉቀዋል።
የስልጣን ርክክቡ የተደረገው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትላንትናው ዕለት መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለት ላለፉት ሁለት አመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የነበሩትን አቶ ጌታቸው ረዳን በይፋ ማሰናበታቸውን ተከትሎ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ “ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል” ብለዋል።
መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
