በሚያፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድን አንገቱ ላይ ጉልበቱን ጭኖ የገደለው ፖሊስ “ድሬክ ቹቫን” በግድያ ወንጀል ተከሰሰ፡፡

የ 46 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ሀሰተኛ የባንክ ፅሑፍ ተጠቅመሀል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ በፖሊስ ድሬክ ቹቫን መገደሉ ከፍተኛ ቁጣን አስነስቷል።

ድርጊቱን የፈፀመው ፖሊስ በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን ከእርሱ በተጨማሪ አብረውት የነበሩ ሌሎች ሶስት መኮንኖች ከሥራ መባረራቸውም ተነግሯል፡፡

ግድያውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህራዊ ትስስር ገፆች ከተለቀቀ ወዲህ የሚኒሶታ ከተማ ከፍተኛ ተቋውሞን አስተናግዳላች፡፡

በሚኒያፖሊስ ላይ የተጀመረው ተቃውሞም በመላው አሜሪካ እየተዛመተ ነው።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሚኒያፖሊስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያን እና ሌሎች ተቋማትን ማቃጠላቸውን እና ተቃውሞው እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል፡፡

ከ170 በላይ የቢዝነስ ተቋማት እንደተዘረፉና ጉዳት እንደደረሰባቸውም ነው የተዘገበው፡፡

የአሜሪካ ብሄራዊ ዘብ ጦርም በከተማዋ እንዲሰማራ ተደርጓል፡፡

ቺካጎ ፣ ሎሳንጀለስ ፣ ሜምፊስ ፣ ቴኔስ እና ኬን-ቱኪ ህዝባዊ ተቃውሞው ከተስፋፋባቸው ግዛቶች መካከል ናቸው፡፡

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከዚህ ቀደም በግፍ ለተገደሉ ጥቁር አሜሪካውያንም ፍትህ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *