በጋዛ የሚገኙ 90 በመቶ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡

በጋዛ ሰርጥ አስፈላጊውን ህክምና ለማግኘት የሚያስፈልጉ የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ 90 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነዉ ሲል የአለም ጤና ድርጅት አስታዉቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ትላንት የተከበረውን የዓለም ጤና ቀን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የጋዛ ሰርጥ ልጅ ሆኖ ለማደግ በጣም አደገኛ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል ብሏል፡፡

እየቀጠለ ባለው ጥቃት ፣ መፈናቀል እና የህክምና አገልግሎት እጦት ምክንያት እርግዝናም በፍርሃት የተከበበበት ሆኗል ሲል ገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ማርጋሬት ሃሪስ፤ በጋዛ የሚገኙ ነፍሰ ጡር እናቶችን ጤና ሲገልጹ፤ ማንኛዉም ሰው ሊገምተው ከሚችለው ከማንኛውም ነገር በላይ የከበደ ነዉ ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ምንም የምግብ ወይም የሕክምና እርዳታ ለጋዛ እየደረሰ አይደለም፤ ቀድሞዉኑም እየተሰቃዩ ላሉ እናቶች እና ህጻናት ሁኔታው ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው፤በጋዛ ውስጥ ከአራት ነፍሰ ጡር እናቶች አንዷ ከባድ የጤና ችግሮች እያጋጠሟት ሲሆን፤ 25 በመቶው ደግሞ በከባድ የደም ማነስ እና 23 በመቶዎቹ ለቅድመ ወሊድ ምጥ ስጋት የተጋለጡ ናቸዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *