አሜሪካ የደቡብ ሱዳናውያንን ቪዛ መንጠቋን ተከትሎ ደቡብ ሱዳን ቅሬታዋን ገለጸች።

የሌላ የአፍሪካ አገር ዜጋን በተመለከተ ክስተት ምክንያት የደቡብ ሱዳናውያን ቪዛ በአጠቃላይ መነጠቁን ደቡብ
ሱዳት ነቅፋለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላዲ ማርኮ ሩቢዮ ደቡብ ሱዳናውያን ቪዛ እንደሚከለከሉ አስታውቀዋል።

ውሳኔውን ያሳለፉት ደቡብ ሱዳን ከአሜሪካ የተባረሩ ዜጎቿን አልቀበልም ብላለች በሚል ነው።

ወደ ደቡብ ሱዳን ከአሜሪካ የተላከው ሰው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጋ በመሆኑ ምክንያት ግለሰቡን
አለመቀበሉን የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል።

“ግለሰቡ ለተጨማሪ ምርመራ ወደተላከበት አገር ተመልሷል” ሲልም አስታውቋል።

ዶናልድ ትራምፕ መልሰው ሥልጣን ከያዙ በኋላ አሜሪካ ቪዛ በመከልከል የአንድን አገር ዜጎች ባጠቃላይ ዒላማ
ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ትራምፕ ስደተኞችን በጅምላ እንደሚመልሱ ሲዝቱ ቆይተዋል።

የደቡብ ሱዳን ዜጎች በአጠቃላይ አሜሪካ እንዳይገቡም የሚታገዱ ይሆናል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *