የሊቨርፑሉ ግብጻዊው አጥቂ ሙሀመድ ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ለተጨማሪ አመት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል።
ቢቢሲ ይፋ እንዳደረገው ሙሃመድ ሳላህ እስከ 2027 በአንፊልድ ለመቆየት ፊርማውን አስቀምጧል።
ሙሃመድ ሳላህ በፒኤስጂ እና በሳውዲ አረቢያ ክለቦች በጥብቅ ሲፈለግ ቢቆይም በመርሲሳይዱ ክለብ መቆየትን ምርጫው አድርጓል።
ሳላህ ለሊቨርፑል 393 ጨዋታዎችን አከናውኖ 243 ጎሎች አስቆጥሯል። 109 ጎል የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል
ጋዲሳ መገርሳ
ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
