በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዲጂታል ሎተሪ ይፋ ሆኗል፡፡ የዲጂታል አገልግሎቱ ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን ያቀረበ ሲሆን በስምንት የሀገራችን ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ይህ ዘመናዊ ሎተሪው ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል “መላ” በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ሚያዚያ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
