ትራምፕ ከሩሲያ ከፍተኛ ጥቃት በኋላ ጦርነት በመጀመሩ ዘሌንስኪን ተጠያቂ አድርገዋል

ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ ጋር ጦርነቱን የጀመረው ዘለንስኪ ነዉ በማለት ወቅሰዋል፡፡

በዩክሬን በደረሰ እና ከባድ ነዉ በተባለ የሩሲያ ጥቃት 35 ሰዎች ሲሞቱ 1መቶ17 ሌሎች ቆስለዋል ።

በሶስት ሰዎች ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ያሉት ትራምፕ፤ ፑቲን የመጀመሪያዉን ሃላፊነት፣ ሁለተኛዉ ምን እንደሚያደርግ እንኳን የማያዉቅ የነበረዉ ጆ ባይደን እና ሶስተኛዉ ደግሞ ዘለንስኪ ናቸዉ ብለዋል፡፡

የትራምፕ አስተያየት ሩሲያ እሁድ እለት በዩክሬኗ ሱሚ ከተማ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ይህም በዚህ ዓመት ሩሲያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያደረሰችዉ እጅግ የከፋ ጉዳት ነዉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሰንፔር እንዳለዉ

ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *