ላብራቶሪውን የሩሲያ የሸማቾች መብት እና የሰብዓዊነት ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ ኃላፊ ዶክተር አና ፖፖቫ ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስረክበዋል።
ሩሲያ ሰር የሆነው ይህ ላብራቶሪ “በሽታን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል” አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ ኃላፊዋ ዶክተር አና ፖፖቫ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።
ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪው የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በማጠናከር በተለይም ተላላፊ በሽታዎችን የመቋቋም አቅም በማጎልበት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የሕክምና መሳሪያው በአንድ ጊዜ 300 በሽታዎችን የመለየት አቅም እንዳለውም ጠቁመዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል ።
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
