ብርሃን ገበያ የገበያ ትስስር የሚፈጥር ፕሮጀክት ሲሆን፤ስልጠና ለወሰዱ የመጀመሪያ ዙር 10 ሺህ ወጣቶች የአነስተኛ ሱፐርማርኬት ባለቤት የሚያደርግ ነው።
በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ ወደ ከፍተኛ የገበያ ማዕከላት ባለቤትነት የማሳደግ ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ያለምንም መነሻ ካፒታል የሚተገበር የዱቤ ሽያጭ ስርዓት መሆኑን የገለፁት የሊንክአስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፊሊሞን ካሳሁን፤ በተለያዩ ክልሎች ከሚሰሩ ተቋማት ጋር የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በገበያ ማዕከላቱ ከቻይና የሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች እንዲሁም ከአምራች ገበሬዎች እና አቅራቢዎች የአትክልት፣የህፃናት ምግቦች እና የተለያዩ ምርቶች ለገበያ ይቀርባሉ።
የክፍያ ስርዓቱም የዲጂታል የክፍያ ስርዓት ሲሆን፤ ዳሽን ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ ባንኮች ጋር በአጋርነት ይሰራል።
ፕሮጀክቱ ከቻይና በተገኘ ድጋፍ በጤግሮስ ትሬዲንግ ፣ ሊንክአስ ትሬዲንግ እና ቻይና የሚገኘው ኢዩ ሸገር ካምፓኒ በጋራ በመተባበር የሚተገብሩት ነው።
ፕሮጀክቱ በአምስት አመት ኮንትራት አርቲስት መሉዓለም ጌታቸውን እና ቅድስት መሉዓለምን የብራንድ አምባሳደር አድርጓል።
እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
