ሺረር -የፒኤስጂው አጥቂ ምባፔ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መጥቶ ቢመለከተው እንደሚወድ ተናግሯል፡፡

ሺረር -የፒኤስጂው አጥቂ ምባፔ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መጥቶ ቢመለከተው እንደሚወድ ተናግሯል፡፡ የቀድሞው የኒውካስል ዩናይትድ አጥቂ አለን ሺረር አንድ ቀን ክሊያን ምባፔ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መጥቶ ቢመለከተው ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል፡፡

ከፈረንሳይ ጋር የዓለም ዋንጫን ያሸነፈው ምባፔ በሊግ 1 ቆይታው በፒኤስጂ ውጤታማ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ስሙ ከሪያል ማድሪድ እና ሊቨርፑል ጋር ተያይዞ ሲጠቀስም ሰንብቷል፡፡ ምባፔ ገና 21 ዓመቱ ቢሆንም ከወዲሁ ሰባት ትልልቅ ዋንጫዎችን አሸንፏል፡፡

የትኛው ፈረንሳዊ አጥቂ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጥቶ ሲጫወት መመልከት እንደሚፈልግ በካናል ፕላስ ሲጠየቅ ሺረር ‹‹ ክሊያን ምባፔ ቢመጣ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ለአንድ ወጣት ተጫዋች እርሱ ላይ የምመለከተው በራስ መተማመን እና ክህሎት እጅግ ያስገርመኛል፡፡ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ ደግሞ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ ለፕሪምየር ሊጉ ተጨማሪ ግብዓት ይሆነዋል›› የሚል ምላሽ ሰትቷል፡፡

ለየትኛው ክለብ ሲጫወት ቢመለከት ደስ እደሚለው ሲጠየቅ ‹‹ ከአንድ ክለብ ውጪ ለእርሱ የሚስማማ ያለ አይመስለኝም፡ ፡ ያ ክለብም ደግሞ ኒውካስል ዩናይትድ ነው›› ብሎ ቀልዷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *