የማሊ ወታደራዊ መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ገደበ፡፡

ከቀናት በፊት በከተማዋ ከተደረገዉ ሰልፍ በኋላ፤ ወታደራዊው መንግስት ‹‹ወደ ፊት እስከምናሳዉቅ ድረስ›› የፖለቲካ ፓርቲዎች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም ሲል አግዷል፡፡

በሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ የተፈረመዉ የትዕዛዝ ወረቀት ፤ ገደቡ በፖለቲካ ላይ የሚሰሩ የትኛዉንም ተቋማት ይመለከታል ይላል፡፡

ይህ ዉሳኔ ባለስልጣናት የፖለቲካ ፓርቲዎችን አሠራር የሚመራውን ህግ መሰረዙን ካወጁ ከአንድ ሳምንት በኋላ የተወሰደ እርምጃ ነዉ፡፡

የፖለቲካ-ወታደራዊ ሽግግሩ ከታህሳስ 31 በፊት በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ለመጠየቅ እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲመለስ በደርዘን የሚቆጠሩ ፓርቲዎች ጥምረት መቋቋሙ ተገልጿል፡፡

ቅዳሜ እለት አዲሱ ጥምረት በዋና ከተማዋ ባማኮ የወታደራዊውን መንግስት እርምጃ በመቃወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አሰባስቧል።

በዚህ ሳምንት መጨረሻም ሌላ ተቃውሞ ተጠብቆ ነበር።

ከተቃውሞ ሰልፍ መሪዎች አንዱ የሆነው ቼክ ኡመር ዱምቢያ በአዋጁ አልተገረምኩም ማለታወቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *