የሩሲያ እና የቻይና መንግስታት ሰፊ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በመተግበር ላይ ይገኛሉ – ብለዋል ቭላድሚር ፑቲን፡፡
ፑቲን ሺ ጂንፒንግ በ80ኛው የድል በዓል ከሩሲያ ጋር ለመሆን በመወሰናቸው አመስግነው፤ በድጋሚ በቻይና ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ሩሲያ ለሺ ጂንፒንግ የሞስኮ ጉብኝት ትልቅ ቦታ ብለዋል፡፡ሩሲያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩት ለሕዝቦቻቸው ጥቅም እንጂ ከሌሎች ሀገራት በተቃራኒ ለመቆም አይደለም ሲሉም ተድምጠዋል። ሺ ሞስኮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጉላቸዋል፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው 80ኛውን የድል በዓል ምክንያት በማድረግ በበዓሉ ላይ በመገኘታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ቻይና እና ሩሲያ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ታሪክ እውነታን ለማስጠበቅ ዝግጁ ናቸው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የሩሲያ እና የቻይና ሐሰዝቦች ከ80 ዓመታት በፊት ታላቁን ድል ለመቀዳጀት ከባድ ዋጋ በመክፈል በዓለም ሰላም እንዲሰፍን እና ለሰው ልጅ እድገት ትልቅ ታሪካዊ አስተዋፅኦ አድርገዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል ።
ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
