የኢትዮጵያ ሴቶች ፕርሚየር ሊግ የ2017 የውድድር አመት ትናንት በሀዋሰ ከተማ ፍፃሜውን አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ያሳካውን ዋንጫ በይፋ ተረክቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቻምፒዮንነቱን ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ፣ ሀዋሳ ከተማ የብር፣ ሲዳማ ቡና የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊ ሲሆኑ ቦሌ ክ/ከተማ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በደማቅ የመዝጊያ ሥነ ስርዓት የ2017 የውድድር ዘመን ፍፃሜውን አግኝቷል።

ሴናፍ ዋቁማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ በ22 ግቦች የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን አጠናቃለች።

በዘንድሮው የውድድር አመት ሀሞበርቾ ዱራሜ እና ቂርቆስ ክፍለከተማ ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዳቸው ተረጋግጧል።

በሌላ በኩል ወደ ፕርሚየር ሊጉ ሸገር ከተማ ሴቶች ቡድን እና ይርጋጨፌ ወደ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *